የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሠራር መመሪያ 683/2013የትራንስፖርት ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 600/2000 በአንቀጽ 5 /አምስት/ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ አሠጣጥ አስመልክቶ በህዳር 2003 ዓ.ም የመጀመሪያውን የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ አሠራር መመሪያ አውጥቶ ለሁሉም ክልል አሰራጭቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከ2004 እስከ 2006 ዓ.ም የተተገበረውን መመሪያ በትግበራው ወቅት የታዩ ክፍተቶችን መሠረት በማድረግ የተሻሻለውንና የቀድሞውን ሊተካ የሚችል በማድረግ የሚከተለውን መመሪያ አውጥቷል፡፡