የንግድ ተሽከርካሪዎች የኪራይ ትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የሚንቀሳቀሱት በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች በመሆኑ አሠራራቸውን እና አደረጃጀታቸውን ወጥና አገራዊ ይዘት እንዲኖራቸው በማድረግ፣ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን ቀልጣፋ፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ፍትሃዊና የተጠቃሚውን የመክፈል አቅም ያገናዘበ እንዲሆን በማስቻል እና ተጠያቂነትን በማረጋገጥ በውድድር ላይ የተመሠረተ አሠራር እንዲኖር ለማድረግ መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የትራንስፖርት ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 468/1997 አንቀጽ 7 ንዑስ አንቀጽ 1 (ረ) መንገደኞች፣ ዕቃዎች፣ ፖስታዎች በንግድ ትራንስፖርት ስለሚጓጓዙበት ሁኔታ መመሪያ ማዉጣትና አፈጻጸሙን መከታተል በተሰጠው ሥልጣን እና ተግባር መሠረት ይህንን አገር አቀፍ የንግድ ተሽከርካሪዎች የኪራይ ትራንስፖርት ደረጃ እና አገልግሎት አሠጣጥ መመሪያ አዉጥቷዋል፡፡