በኢትዮጵያ ፈጣን የከተሞች መስፋፋትን ተከትሎ የከተማ ነዋሪዎችንና የሌሎች ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማጠናከር መልካም ተሞክሮዎችንና ልምዶችን በማስፋፋት የከተማ ልማት ፖሊሲውን፣ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን ትግበራና ስኬት ማፋጠን ይቻል ዘንድ አመታዊ የከተሞች ሳምንት የተሰየሙ ሲሆን፣ በዚሁም መነሻነት ቀደም ሲል አንደኛው፡ ሁለተኛው ሶስተኛው እና አራተኛው የከተሞች ሳምንት በተለያዩ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን በተመሳሳይ መልኩ ኛዉ የኢትዮጵያ ከተሞች ሳምንት በባህር ዳር ከተማ ከህዳር 11- 17 ቀን 2005 ዓ.ም ይከበራል፡፡
እንደሚታወቀው ማንኛውም ተቋም የተሰጠውን ተግባርና የተጣለበትን ኃላፊነት በሚገባ ሊያከናውን የሚችለው የተጠናከረ የገቢ ምንጭና በትክክል የተደራጀ የፋይናንስና አቅርቦት አመራር ስልት ሲኖረው መሆኑ አጠያያቂ አይደለም፡፡ የተደራጀና የተጠናከረ የፋይናንስና አቅርቦት አመራር ሲባል አንድ ተቋም የሚሰበስበውን ገቢ የሚያወጣውን ወጪና አቅርቦት እንዴት በተግባር ላይ እንደሚያውለው የሚከተለው የአሠራር ስልት ማለት ነው፡፡ ለዚህም የፋይናንስ ዕቅድና የፋይናንስ አያያዝ መመሪያዎችን እንዲሁም የአቅርቦት አፈጻፀም መመሪያ ማዘጋጀትና ሥራ ላይ ስለሚውልበት ሁኔታ አመቺ ስልት መቀየስ የተሟላና ተገቢ ይሆነ የሒሳብና የአቅርቦት መዝገብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም 5ኛውን የኢትዮጵያ የከተሞች ሳምንት ዝግጅት በአግባቡ ለማካሄድ የሚሰበሰበውን ገንዘብ በኃላፊነት እንዲመራ የተደራጀ ኮሚቴና የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች ሥራቸውን ሲያከናውኑ የሚፈለግባቸውን ተግባር ጠንቅቀው ሊያውቁ ይገባል:: ከዚህ አኳያ የሚያከናውኑትን የዕለት ተዕለት ሥራ በአግባቡ ለማከናወን የሚረዳ የፋይናንስና ሎጂስቲክ የአቅርቦት አፈፃፀም መመሪያ ሊኖር ይገባል። በዚህም መሠረት ይህ አጭር የፋይናንስና ሎጂስቲክ የአቅርቦት አሠራር መመሪያ ተዘጋጅቷል።