የመመሪያ መለያ: 343/2013
ቀን: ታህሳስ 13፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

ለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የሚውሉ ግብዓቶችን ወደ ሀገር ውስጥ ስለማስገባት የወጣ ጊዜያዊ የአስተዳደር መመሪያ ቁጥር 343/2013

የኮሮና ቫይረስ በዓለም ዓቀፍናበሀገር ደረጃ እየተሰራጨ ያለ በሽታ ከመሆኑ አንፃር ህብረተሰቡ ላይ የበለጠ አደጋ ከማድረሱ በፊት አስቀድሞ መከላከል አስፈለጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ለኮረና ቫይረስ የሚውል ግበዓት ለማስመጣት የሚፈልግ አካል ቁጥጥር የተቀላጠፈ እንዲሆንና ህብረተሰቡ በቀላሉ ምርቶቹን በገበያ ላይ እንዲያገኝ ለማድረግ በመግቢያና መውጫ ኬላዎች የሚደረግን የቁጥጥር ሂደት ቀልጣፋ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የኮሮና ቫይረስ ለራስ መከላከያና ሌሎች ቫይረሱን ለመቆጣጠር የሚያስፈልጉ ግብዓቶች ወደ ሀገር ውስጥ የማስመጣት ተግባር ሕግን በአከበረ ሁኔታ የአሠራር ሥርዓትን ተከትሎ እንዲከናወን ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፤

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣንለኮሮና ቫይረስ የሚውሉ ግበዓቶች ጥራት፣ ደኅንነትና ፈዋሽነት በማረጋገጥ ረገድ የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀጽ 71(2) መሠረት ይህን ጊዜያዊ የአሠራር መመርያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

Ethiopian Food and Drug Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration