የኮመኒኬሽን አገልግሎቶች ከተቀመጠው የደረጃ ጥራት ጋር መጣጣማቸውን ለማጋገጥ የሚሰጡ የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶችን የቴክኒክ ደረጃ መለየት አስፈላጊ ሆኖ በማገኘቱ፤
በቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተሮች የሚሰጡት የአገልግሎት ጥራት በተቀምውጡ መለኪያዎች እና በመለኪያ ዘዴዎች ላይ በመርኮዝ እንዲሆን፣ ሪፖርት እንዲደረግ እና እንዲታተም የሚያስችል የአገልግሎት ጥራት ማዕቀፍ መዘርጋት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተሮች ማሟላት ያለባቸውን የአገልግሎት ጥራት ግዴታዎች ለቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሸማች የማቅረብ አስፈላጊነትን በመገንዘብ፤ የ ተሻሻሉ የኔትዎርክ ትስስር እና ክዋኔ እንዲኖር የሚያስችሉ ዝቅተኛ መለኪያዎች ማስቀመጥ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፣
የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 1148/2011 አንቀጽ 6(2)፤ 6(5) እና 54(2) መሠረት ይህንን የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ጥራት መመሪያ አውጥቷል፡፡