የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት የጥራት ደረጃን ለማረጋገጥ የተለያዩ ቴክኒካዊ እና ቴክኒካዊ ያልሆኑ ተግባራትን ማከናወን የሚያስፈልግ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ አንዱ የአገልግሎት ጥራትን የተመለከተ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ነው።
የቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተሮች የሚሰጡት አገልግሎት የተቀመጠለትን የጥራት ደረጃ ማሟላት አለበት፡፡ ለዚህም የጥራት ደረጃውን በግልጽ የሚያመለክቱ መመሪያዎች እና ስታንዳርዶች የሚያስፈልጉ ሲሆን ይህም ባለስልጣኑ የአገልግሎት የጥራት ቁጥጥር ስራን ለመሥራት እና ተፈጻሚ ለማድረግ ያስችለዋል፡፡
ይህንም መሠረት በማድረግ ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት ጥራት መመሪያን ያዘጋጀ ሲሆን ይህም በዘርፉ ውጤታማ ስራን መሥራት ያስችላል ተብሎ ይታመናል።