የመመሪያ መለያ: 796/2013
ቀን: ጥቅምት 29፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የቴሌኮሙኒኬሽን ሙግት መፍቻ መመሪያ ቁጥር 796/2013 ማብራሪያ

በቴሌኮመኒኬሽን አገልግሎት አሰጣጥ እና አጠቃቀም ላይ የተለያዩ ቅሬታዎች ሊነሱ ይችላሉ። እነዚህ ቅሬታዎች በቴሌኮም አገልግሎት ሰጪዎች እና በአገልግሎት ተቀባዮች እንዲሁም በቴሌኮም አገልግሎት ሰጪዎች መካከል ሊሆን ይችላል። እነዚህን ቅሪታዎች በባህሪያቸው ቴክኒካል እና ውስበስብ ሲሆኑ መደበኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን አስቸጋሪ ሊሆንበት ይችላል። በዚህም ምክንያት እነዚህን እና መሰል አለመግባባቶች ለመፍታት አንድ አንድ ሃገራት ጉዳዩን የሚመለከቱ ልዩ ችሎቶችን የሚመሰርቱ ሲሆን ሌሎች ሃገራት ደግሞ ይህን ሥልጣን ለቴሌኮም እና ኢንተርኔት ተቆጣጣሪ አካል ሲሰጡት ይስተዋላል። ይህ አካሄድ በአንደ በኩል ፈጣን እና እውቀት መር ውሳኔን መውሰን የሚያስቸል ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የተከራካሪ አካላት እንግልትን ያስቀራል።

በዚህም መሠረት በኮሚኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 1148/2011 አንቀጽ 6(15) ላይ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አፕሬተሮች እና በተጠቃሚዎች እንዲሁም በኮመኒኬሽን አገልግሎት ኦፕሬተሮች መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን የማየት፥ የመመርመር እንዲሁም ለአለመግባባቶች ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ተሰጥቷታል።

እነዚህ የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነት ለመወጣት አስቻይ የሆኑ ሁኔታዎች መፈጠር ያለባቸው ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የሕግ ማዕቀፎች ቀርጿ ወደ ተግባር መግባት ነው። ይህንን ሕሳቤ በመያዝ ይህ መመሪያ የተዘጋጀ ሲሆን በዘርፉ ውጤታማ ስራን መሥራት ያስችላል ተብሎ ይታመናል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን

Ethiopian Communication Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration