ጸረ ውድድር በሆኑ ባህሪያት ወይም ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ወይም ሊሳተፍ ይችላሉ የሚሉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተሮችን ማየት የሚያስችል ማዕቀፍ ማዘጋጀት በማስፈለጉ፤
አግባብነት ያለው ገበያን ውሰን እና አግባብነት ባለው ገበያ ውስጥ ጉልህ የገበያ ድርሻ ያለው ኦፕሬተርን መሰየም አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ፤
የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎቶች በብቸኝነት እንዳይያዙ ማድረግ እና በቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተሮች መካከል ወድድር እንዲኖር ማበረታታት አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት፤ የቴሌኮሙኒኬሽን ኦፕሬተር ውህደት ወይም የባለቤት ግዢን በተመለከተ ግምገማ ለማድረግ እና መወሰን የሚያስችል ማዕቀፍን ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ፤
በኮሙኒኬሽን አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 1148/2019 አንቀጽ 6(2)፣ 47 እና 54(2) መሠረት ባለሥልጣኑ ይህንን የቴሌኮሙኒኬሽን ወድድር መመሪያ አውጥቷል፡፡