የመመሪያ መለያ: 217/2013
ቀን: ኅዳር 22፥ 2004 ዓ.ም.
Language: Amharic

ለውጭ ገበያ በሚቀርብ ጥሬ እና በከፊል የተዘጋጀ ቆዳና ሌጦ ላይ የተጣለውን ታክስ ለማሻሻል የወጣ መመሪያ ቁጥር 217/2013

በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዘርፍ የተሠማሩ ኢንዱስትሪዎች ለውጭ ገበያ የሚያቀርቡት ምርት ደረጃ ተሻሽሎ አገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ ከፍ እንዲል ለማድረግ ለውጭ ገበያ በሚቀርብ በከፊል የተዘጋጀ ቆዳና ሌጦ ላይ ታክስ የተጣለ በመሆኑ፣

የታክሱ መጣኔ አነስተኛ በመሆኑ ምክንያት ከፍተኛ መጠን ያለው ቆዳና ሌጦ በከፊል በተዘጋጀ (በክረስት) ደረጃ ለውጭ ገበያ የሚላክ ሲሆን፣ ይህ ሁኔታ በአገር ውስጥ የጥሬ ቆዳና ሌጦ አቅርቦት እጥረት እንዲኖር ያስከተለውን የዋጋ ያለመረጋጋት ማስወገድ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

እሴትን ከመጨመር እና የሥራ ዕድልን ከመፍጠር አኳያ የጎላ አስተዋፅዖ የሚኖረውን የቆዳ ውጤቶች ኢንዱስትሪ ልማት ለማስፋፋት ኢንቬስትመንት ለመሳብ የሚያስችልና አስተማማኝ ያለቀለት ቆዳ አቅርቦት መፍጠር በማስፈለጉ፣ በክረስት ደረጃ ለውጭ ገበያ እየቀረበ ያለው ቆዳና ሌጦ ተገቢውን ዋጋ እያገኘ ባለመሆኑ የእሴት ጭማሪ በሚያስገኙ የምርት ሂደቶች ውስጥ እንዲያልፍ በማድረግ ባለቀለት ቆዳ ወይም በቆዳ ውጤቶች መልክ ለውጭ ገበያ በማቅረብ አገሪቱ ከንዑስ ዘርፉ የምታገኘው የውጭ ምንዛሪ እንዲጨምር ማድረግ ተገቢ በመሆኑ፣ ከዚህ የሚከተለው መመሪያ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የገንዘብ ሚኒስቴር

Ministry of Finance

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration