የተማሪዎችንና የምገባ ማዕከልን ግብዓት ወይም ቁሳቁስ አቅርቦት እና ስርጭት የሚመራበት ህጋዊ ስርዓት በመዘርጋት ውጤታማ የግብዓት አቅርቦትና ፍትሀዊ ስርጭት በማስፈለጉ፣ በግዢ እና ከተለያዩ አካላት በስጦታ ወደ ኤጀንሲው የሚገቡ ለተማሪዎችና ለምገባ ማዕከሉ የሚሆኑ ግብዓት ወይም ቁሳቁስ ከብክነት በፀዳ፣ ግልጽና ወጥ የሆነ የመንግሥት የንብረት አስተዳደር አሠራር ሥርዓትን ለመዘርጋት፣
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምገባ ኤጀንሲን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡