ለፌደራል ይቅርታ ቦርድ የሚቀርቡትን የይቅርታ ጥያቄዎች በተፋጠነ መልኩ ለማስተናገድ ይቻል ዘንድ የይቅርታ ጥያቄ ማመልከቻዎች አሟልተው መያዝ የሚገባቸውን መረጃዎች በግልጽ ማመላከት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤
የፌደራል የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አሰጣጥና አፈጻፀም ስነ-ሥርዓት አዋጅን ለማስፈጸም ወጥቶ የነበረዉ መመሪያ ዝርዝር መስፈርቶችን ያላስቀመጠና ግልጽ ባለመሆኑ፤
ታራሚዎችን የሚመለከት አስተያየት መረጃና ምስክርነት ከሚሰጡ ተቋማትና ግለሰቦች የሚፈለገውን ዝርዝር መረጃ በግልጽ ማስቀመጥና እንዲሁም የቦርድ አባላትም አዋጁን በአግባቡ ለማስፈፀም የሚያስችላቸውን ስነ-ሥርዓት መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በይቅርታ አሰጣጥና አፈጻጸም ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 840/2006 አንቀጽ 28/2/ መሠረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡