ኢትዮጵያ ለዘመናት ስትጠቀስበት የ ቆየው ድህነትና ኋላቀርነት በአሁኑ ወቅት እየተቀየረ ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት ከሚያስመዘግቡ ሃገራት ጋር እየተጠራች ትገኛለች።
ይህ ኢኮኖሚያዊ እድገት እውን የሚሆነው ቀጣይነት ካለው ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ልማት ጋር ሲቀናጅ ነው። በመሆኑም ልማት ሁሉን አቀፍና የተቀናጀ መሆን ይጠበቅበታል።
ስለዚህ ነው መንግሥት በየዘርፉ ያለ ችግሮችን ለመቅረፍ ልዩ ልዩ ፖሊሲዎችን ነድፎ እየሰራ የሚገኘው፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ለባህልና ኪነ ጥበብ የ ፖሊሲ ድጋፍ በማድረግ የ ሀገራችን ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባህል፣ ትውፊት እና ታሪክ ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ እንዲያገኙ የ ተቻለውን እያደረገ ይገኛል፡፡
‹‹ኢኮኖሚያዊ እድገት ያለማኅበራዊ ልማት ብቻውን ዘላቂነ ት አይኖረውም›› የሚለውን መርህ በመከተል መንግሥት ለባህልና ስነ ጥበብ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡ በሂደትም በየዘርፉ ያለትን ክፍተቶች ለመሙላት ልዩ ልዩ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህ አንደ የባህል አምባሳደር ለሆኑት የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ክብራቸውን የሚመጥን የሙያ ማበረታቻ ክፍያ እንዲያገኙ መንግሥት የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ነው፡፡