የስፖርት ውርርድ ሎተሪን ጥብቅ በሆነ ሕግና ስርዓት እንዲመራ ማድረግና ቁጥጥሩን ማጠናከር በማስፈለጉ፣
ቀደም ሲል በነበረው መመሪያ ያልተካተቱ ተጨማሪ ክልከላዎች ማካተት በማስፈለጉ፣
የአዲስ ፈቃድ ማውጫ፣ የፈቃድ እድሳት ክፍያና የማኅበራዊ አገልግሎት ክፍያ ማሻሻል በማስፈለጉ፣
የአለም የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ህጎች ከደረሰቡት የእድገት ደረጃ ጋር ተቀራራቢ ለማድረግና በአወራራጁና በተወራራጁ መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን ለመፍታት የሚያስችል መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ የገቢዎች ሚኒስቴር የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን እንደገና ለማቋቋም በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 160/2001 አንቀጽ 21 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ፈቃድ መመሪያ ቁጥር 83/2005ን በዚህ መመሪያ አሻሽሏል፡፡