የመመሪያ መለያ: 140/2013
ቀን: ጥቅምት 1፥ 2005 ዓ.ም.
Language: Amharic

የስፖርት ውርርድ ሎተሪ መመሪያ ቁጥር 140/2013

በአገራችን የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮች መዘውተር ከጀመረ ቆየት ያለ ሲሆን በተጨማሪ በአገሪቱ በሰፊው እየተስተዋለ ካለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ጋር በተያያዘ በስፖርቱም ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ መነቃቃት እየታየ በመሆኑ፤

ዘመኑ ባፈራው በዲኤስቲቪ /dstv/ የሚተላለፉ የአውሮፖ የእግር ኳስ ውድድሮች በይበልጥ ለወጣቱ እንደዋነኛ የጊዜ ማሳለፊያና መዝናኛ በመሆን እያገለገለ የሚገኝ በመሆኑ ስፖርታዊ ውድድሮችን መሠረት ያደረጉ የዕድል ሙከራ ጨዋታዎች በስፋት እየተዘወተሩ መምጣታቸውና ህብረተሰቡም በእነዚህ የዕድል ጨዋታዎች ለመሳተፍ ያለው ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ በዘርፉ ፈቃድ አውጥተው ለመሰማራት የሚፈልጉ ግለሰቦች/ድርጅቶች ጥያቄ እየተበራከተ በመምጣቱ እና በደንብ ቁጥር 160/2001 አንቅጽ 12 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የስፖርት ውርርድ ሎተሪ ፈቃድ በማውጣት ሊያካሄዱ እንደሚችሉ በመደንገጉ፤

ሥራውን በሕግ አግባብ የበለጠ ግልጽና ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ለመምራት ተገቢ በመሆኑ የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደርን እንደገና ለማቋቋም በወጣው ደንብ ቁጥር 160/2001 አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት የሎተሪ ሥራን የማካሄድ፣ የማስተዳደርና የመቆጣጠር እንዲሁም በሕግና በስርዓት እንዲመራ የማድረግ ሥልጣን ለአስተዳደሩ በመሰጠቱ ከላይ በተጠቀሰው ደንብ ቁጥር አንቀጽ 21 መሠረት ደንቡን ለማስፈጸም የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ይህን የስፖርት ውርርድ ሎተሪ መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን

Ethiopian Revenue and Customs Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration