የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር በፌዴራል ደረጃ ለሚቋቋሙ የስፖርት ማህበራት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 917/2008 አንቀጽ 37/1//በ/ ስር የደነገገ በመሆኑ፤ መንግሥት በፌዴራል ደረጃ ለተቋቋሙ የስፖርት ማህበራት በየዓመቱ የበጀት ድጋፍ የሚያደርግ በመሆኑ እና ይህ የድጋፍ በጀት ግልጽና ፍትሀዊ በሆነ የአሠራር ቀመር የሚደለደልበትን ሁኔታ ማመቻቸት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ ማህበራቱ ከመንግሥት የሚያገኙትን የበጀት ድጋፍ ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው አሠራር ለታቀደለት ዓላማ ማዋልቸውን ማረጋገጥ ተገቢ በመሆኑ፤ እነዚህን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡