የተለየ ድጋፍ የሚያስፈስጋቸው የሕ/ክፍሎች እንደማንኛውም ዜጋ ሁሉ በሕግ ፊት እኩል ተጠቃሚነት ቢኖራቸውም በጉዞ ላይ የሚደረግላቸው ድጋፍ ባለመኖሩ የትራንስፖርት አገልግሎት በእኩል መጠቀም አልቻሉም። በመሆኑም በሕዝብ ትራንስፖርት ከቦታ ቦታ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሂደት የሚገድቡ በርካታ ችግሮችና ተፅዕኖዎች ሲደርሱባት ይስተዋላል፡፡
በመሆኑም የተለየ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የሕ/ክፍሎች የትራንስፖርት አገልገሎት ለማግኘት በሚፈልጉበት ጊዜ በትኬት አቆራረጥ፤ በመናኸሪያ አገልገሎት፤ በጉዞ ላይ የሚያስፈስጋቸውን ደጋና አገልግሎት አሠጣጥ እንዲሁም በትራንስፖርት አገልገሎት አሠጣጥ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመስየት የአጭርና የረጅም ጊዜ የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ አስፈስጓል፡፡