የመመሪያ መለያ: 87/2013
ቀን: ኅዳር 1፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ስትራቴጂ የአፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 87/2013

ትምህርት ሰረታዊ ሰብዓዊ መበት ነ ው፡፡ ዘላቂነት ያለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማን ዕውን ለማድረግ የማያስችልም ትክ የለሽ መሳሪያ ነ ው፡፡ ይህንን ዕውነታ የተገነዘበው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሰት በጾታ፣ በአካላዊ ሁኔታ ቋንቋ፤ ማበራዊና ኢኮኖማዊ ደረጃ፤ ሃይማኖት፤ ወዘተ ልዩነቶች ያልተገደበ ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ በቁርጠኛነት እየሰራ ይገኛል፡፡ አካል ጉዳተኞች እንደ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ሁሉ የትምህርትና ሥልጠና አገልግሎቶች ዕኩል ተጠቃሚ መሆናቸውን ከሚጋገጥ አኳያ መንግሥት የሕግና የፖሊሲማ ቀፎችን ቀርፆ ስራ ላይ ማዋሉ የቁርጠኛነቱ አንድ ማሳያ ነው፡፡

በዚህ ማረት የኢትዮጵያ ህገመንግሥት ትምህርት የሁሉም ዜጎቸ ማኑን ከሚጋገጠም በላይ ባለፉት መንግስታት ከልማት ተገልልው ለኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች የፌዴራል መንግሥት ልዩ የሀብትና የመድጋፍ እንደማደርግላቸው ይደነግጋል፤ በተለይም የህገመንግስቱ አንቀጽ 41 እና 91 መንግሥት የመልሶ ማቋቋምና የድጋፍ አገልግሎቶችን ለአካል ጉዳተኞች የስጠት ኃላፊነት እንዳለበት ይገልፃሉ፤ ከዚህም በላይ፤ መንግሥት ከአካቶ ትምህርት ጋር አግባብነት ያላቸውን ልዩ ልዩ ዓለምዐቀፍ ድንጋጌዎች፤ ኮንቬንሽኖችና ደንቦች በተለይም ለአካቶ ትምህርት አፅንኦት የሰጠውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን የ2006 (እኤአ) የአካል ጉዳተኞች መበቶች ጥበቃ ኮንቬንሽንን ተቀብሎ በማፅደቅ የአገሪቱ ህገመንግሥት አካል እንዲሆኑ አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ በ1986 ዓ.ም ፀድቆ በተግባር ላይ የዋለው የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ ጥራት ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ማዳረስ ዋስትና መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ይገልፃል፡፡ ከዚህም ለሁሉም ሕፃናት እንደሚጥና ከትምህርት ዘርፍ ልማት እንደማረግ ያረጋግጣል፡፡ የአካል ጉዳተኞች ትምህርትን የመበት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ልማትን የሚጋገ ጫ በተጨሄ ፖለሲው ትምህርት ያለ አንዳች አድልዎ ተገልለው ለኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ልዩ ድጋፍ
በተመለከተም ፖሊሲው

• ልዩ ፍላጎት ያላቸው ሕፃናት ከፍላጎታቸውና ከዕምቅ ችሎታቸው ጋር የተጣመ ትምህርት እንደሚሰጣቸው (ቁጥር 2.2.3)፤

• ለልዩ ፍላጎት ትምህርት የሚያስፈልጉ የ ድጋፍ ግብዓቶች እንደሚሉ (ቁጥር 3.7.6) እና

• የልዩ ፍላጎ ት ትምህርት ባለመያዎች በመደበኛው የመምህራን ትምህርት ፕሮግራም እንደሚለጥኑ (ቁጥር 3.4.9.) በግልፅ ያክታል፡፡

የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲውን ማረት በማድረግም ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርትን ልዩ ፍላጎት ላላቸው ሕፃናትና ለተዘነጉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም ስትራቴጂበ1998 ቀርፆ እስከ 2003 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል፤ ስትራቴጂው በስራ ላይ በዋለባቸው 5 ዓመታት ከተገኙ ጥቂት ውጤቶች መካከልም የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራሞች በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መጀመራቸው የ አቅም ግንባታ ሥልጠናዎች መካሄዳቸው የተወሰኑ ሪሶርስ ማከላት መቋቋማቸውና የ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መከናወናቸው ለአብነት ያህል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ይሁንና ስትራቴጂው በነበሩት ወስጣዊ ድክመቶችና በትግበራ ወቅት ባጋጠሙ ችግሮች ምክንያት የ ታለማ ትን ግቦች ማካት አልቻለም ፡፡

ስለሆነ ም ትምህርት ሚኒስቴር ጉዳዩ የሚከታቸው ባለድርሻ አካላት ባሳተፈ ኩ የ 1998ቱን ስትራቴጂ በማሻል የተጠናከረ የልዩ ፍላጎት /አካቶ ትምህርት ስትራተጂ በ2004 ዓ.ም. ነድፏል፡፡ በቀጣይነትም ስትራቴጂወን ስራ ላይ ማዋል ይቻል ዘንድ ይህን የአተገባበር መመሪያ አዘጋጀቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የትምህርት ሚኒስቴር

Ministry of Education

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration