የመመሪያ መለያ: 22/2013
ቀን: ጥር 13፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የደረቅ ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ኡደት ማህበራት አደረጃጀትና የአሰራር መመሪያ ቁጥር 22/2013

በከተማችን አዲስ አበባ የሚመነጨውን ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ በመለየት ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል የማድረግ መልካም ጅማሬዎች ሲኖሩ ለማሳያነትም የሀይላንድና የወረቀት ደረቅ ቆሻሻዎችን በተሻለ ሁኔታ የገበያ ትስስር በመፍጠር የጽዳት ማህበራት እየለዩ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት የማዋል ተግባር እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ነገር ግን በከተማው ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ አብዛኛውን ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት ማዋል የሚቻል ቢሆንም አሁንም በከተማው የሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ በሚፈለገው ደረጃ እየተለየ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት ማዋል ባለመቻሉ አብዛኛው ደረቅ ቆሻሻ ወደ ማስወገጃ ቦታ እየተጓጓዘ እንዲወገድ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በተለይ በከተማው በርካታ መጠን ያለው ስብርባሪ ጠርሙስ፤ መስታዎትና የብርጭቆ፤ አሮጌ ማዳበሪያ ቀረጢት፤ አሮጌ ወረቀትና ካርቶን፤ ጀሪካን ቁርጥራጭ፤ ውድቅዳቂ ብረታ ብረት፤ አሮጌ የኤላክትሮኒክስ እቃዎች ወዘተ በአግባቡ ተለይቶ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግልት እየዋለ አይገኙም፡፡

እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን ደረቅ ቆሻሻዎች በአግባቡ በመለየትና በመሰብሰብ ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት እንዲውል በማድረግ በዘርፉ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል ሲሆን በተጨማሪም ደረቅ ቆሻሻን ወደ ሀብትነት በመለወጥ ለሀገር የሚያበረክተውን ሀገራዊ ፋይዳ ማሳደግ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ደረቅ ቆሻሻን በስፋት ለመልሶ መጠቀምና ኡደት አገልግሎት ለማዋል ያስችል ዘንድ በመልሶ መጠቀምና ኡደት ዘርፍ ብቻ የሚሰማሩ አዳዲስ ማህበራትን አደራጅቶ በዘርፉ ለማስገባት የሚያስችል ይህ የመልሶ መጠቀምና ኡደት የማህበራት አደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የደረቅ ቆሻሻ አስተዳዳር ኤጀንሲ የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር

Addis Ababa City Administration Solid Waste Management Agency

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration