የመመሪያ መለያ: 114/2014
ቀን: ጥር 18፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ መመሪያ ቁጥር 114/2014

የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ፣ የትርጉም አረዳድ እና አተገባበር ላይ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ፈጻሚዎች የግንዛቤ ልዩነት፣የዝግጁነትና የአፈጻጸም ችግር በመኖሩ በሥራ ፈላጊዎችና በኢንተርፕራይዞች እና ኢንዱስትሪዎች ተገቢውን ድጋፍ በሚፈለገው ደረጃ አለመሰጠቱ በዘርፉ እድገት ላይ የሚያስከትለውን ተግዳሮት ለመፍታት የአሠራርስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፤

አገልግሎትን መስጠት የሚገባቸው ተቋማት ከአሁን በፊት የነበሩባቸውን ከአደረጃጀት፣ ከአሠራር፣ ከሠው ኃይል እና ከግብዓት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዮች በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በተቀናጀ ሁኔታ መስጠት እንዲችሉ ለማድረግ ሁሉም ተቋማት አገልግሎቶቻቸውን ተገልጋይ ተኮር ለማድረግና ያስቀመጡትን ግብና ዓላማ ለማሳካት፣ የገቡትን የዜጎች ስምምነት ሰነድ ለማስፈጸም የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

ሁሉም የአንድ ማዕከል አገልግሎት ባለድርሻ አካላት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርየሥራ፣ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርአስፈፃሚ አካላት ሥልጣና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (15) መሠረት ለሥራው ቅልጥፍና ሲባል በአንድ ማዕከል የሚሰጡ አግልግሎቶችን በውክልና የሰጡ በመሆኑ በአንድ ማዕከል የሚሰጠውን አግልግሎት አሰጣጥ የሚመራበትን አሠራር መወሰን በማስፈለጉ፤

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ፣ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት ሥልጣና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ

Addis Ababa City Administration Industry Development Bureau

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration