በገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የማህበረሰቡን የፋይናንስ ንቃተ-ህሊና በማዳበር የቁጠባ ባህል በማሳደግ የአባላትን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የፋይናንስ አገልግሎቶች በቅርበት፣ በጥራት እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የፋይናንስ ተደራሽነት ማሳደግ በማስፈለጉ፤
የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የአባላትን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የተለያዩ የቁጠባ አገልግሎቶችን በመቅረጽና በማስፋፋት ተደራሽ እንዲሆኑ እና የሚሰጡ አገልግሎቶችን ጥራት፣ ቅልጥፍና እና ተመጣጣኝነት መቆጣጠር በማስፈለጉ፤
የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት የሚሰጡት አገልግሎት የአባላትን ፍላጎት እና የአከባቢውን ሀብት መሠረት በማድረግ የተለያዩ የብድር አገልግሎቶችን በመቅረጽ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ በቅርበትና በወቅቱ እንዲሰጡ ለማድረግ እና የአገልግሎቱን ውጤታማነት መረጋገጥ በማስፈለጉ፤
የቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበራት እና አባላት ከሚያከናውኑት ተግባር ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን የአደጋ ሲጋት በመቀነስ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ የአነስተኛ ኢንሹራንስ አገልግሎት በመቅረጽ አገልግሎት መስጠት በማስፈለጉ፤
የማህበረሰቡን የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ እንዲቻል የአባላትን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የወለድ አልባ የፋይናንስ አገልግሎት በመቅረጽና በማስፋፋት አገልግሎቱን ለሚፈልገው የሕብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ማድረግ በማስፈለጉ፤
በኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 985/2009 አንቀጽ 76(3) መሠረት በማድረግ የኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡