የፕራይቬታይዜሽንና የመንግሥት የልማት የሚያስተዳድራቸውን ድርጅቶች ወደ ግል ይዞታ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ድርጅቶች ለማዘዋወር በቅድሚያ የእያንዳንዱ ድርጅት ወይም አክሲዮን ማኀበር ጠቋሚ የንግድ ወይም የንብረት ዋጋ ትመና እንደሚሠራ ይታወቃል፡፡
ከዚህ አኳያ ላለፉት 3 ዓመታት ቢያንስ አንድ ጊዜ ትርፋማ የሆኑት የልማት ድርጅቶች ወይም አክሲዮን ማኀበራት ዋጋ ትመና የሚካሄደው ወደፊት ሊያስገኙ የሚችሉትን ጥቅም ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የንግድ ዋጋቸውን (Business Value) እና የንብረት ዋጋ ትመና በመሥራትና የሁለቱን ዋጋ ትመና በማነጻጸር የተሻለውን ዋጋ በመውሰድ ሲሆን፣ ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ከሣሪ የሆኑ ድርጅቶች ደግሞ የዋጋ ትመና የሚሠራው የቋሚ ንብረቶችንና ክምችቶችን ዋጋ በመተመን ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ኤጀንሲው እየተጠቀመበት የሚገኘው የዋጋ ትመና መመሪያ በመጋቢት 13 ቀን 1996 ዓ.ም. በፕራይቬታይዜሽን ቦርድ የጸደቀውን ሲሆን ይህ መመሪያ ለዋጋ ትመና የሚሆኑ ዝርዝር ጉዳዮችን ያልያዘ ከመሆኑም በተጨማሪ አንዳንድ በየጊዜው የሚፈጠሩ ጠቃሚ ጉዳዮችን ማካተት ተገቢ መሆኑ ግንዛቤ በመገኘቱ ነው፡፡ ስለሆነም የዋጋ ትመና መመሪያ በቋሚ ንብረቶች ፣ በንግድና በርክክብ ወቅት በሚደረጉ የዋጋ ትመናና ማስተካከያዎች ላይ ትኩረት በመስጠት በቦርድ እንዲሻሻል ተደርጓል።