የመመሪያ መለያ: 154/2013
ቀን: ሐምሌ 1፥ 2009 ዓ.ም.
Language: Amharic

ለተጨባጭ መረጃ አቅራቢ ስለሚሰጥ ሽልማት የወጣ መመሪያ ቁጥር 154/2013

በአገራችን እያደገ ከመጣው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የግብር እና የታክስ ከፋዮች ቁጥር መጨመሩን መሠረት በማድረግ ለገቢ ሰብሳቢው ባለሥልጣን ትክክለኛ ገቢያቸውን አስታውቀው ግብር እና ታክስ የሚከፍሉ የመኖራቸውን ያህል በተቃራኒው ግብር ታክስ የመክፈል ግዴታን ላለመወጣት የሚደረግ ጥረት እየረቀቀና እየተወሳሰበ በመምጣቱ፤

በቀድሞው የገቢ ግብር አዋጅ መሠረት በገቢ ግብር ስወራ ላይ ብቻ ሽልማት የሚሰጥበት ሁኔታ በአዲሱ የፌደራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ሽልማት የሚከፈልበት የግብር ታክስ ስወራ እና ማጭበርበር እንዲሆን የተደነገገ በመሆኑ እንዲሁም የሽልማት ሽፋኑ የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ እና የታክስ ህጎችን እንዲሸፍን ማድረግ በማስፈለጉ፣

ግብር እና ታክስ ላለመክፈል እና ግዴታን ላለመወጣት የሚደረግ ጥረትን ባለሥልጣኑ ብቻውን በሚያደረገው ክትትል መቆጣጠር አዳጋች በመሆኑ፣ ድርጊቱ ሊያስከትል የሚችለውን ጉዳት በመቀነስ የግብር እና ታክስ ስወራ እና ማጭበርበርን በመከላከል ባለሥልጣነ ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ገቢ ትክክለኛውን ገቢ ለመሰብሰብ ይችል ዘንድ፤

ግብር እና ታክስ በሚሰውር፣በሚያጭበረብር፣ አሳንሶ በሚያስታውቅ፣ ያላግባብ ተመላሽ በሚወስድ እና እንዲሁም በማንኛውም ህገወጥ ዜዴ የሚያጭበረብር ግብር እና ታክስ ከፋይ ላይ መረጃ ሲቀርብ ለተጨባጭ መረጃ አቅራቢዎች የሚሰጠው ሽልማት አሰጣጥ ለኪራይ ሰብሳቢነት የተጋለጠ እንዳይሆን በማድረግ አሰራሩ በግልጽነት እና ተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፣

ባለሥልጣኑ በፌደራል የታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/08 አንተዕ 134 ንዑስ አንቀጽ (3) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን

Ethiopian Revenue and Customs Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration