በአሁኑ ጊዜ በዓለም ገበያ ያለቀለት ቆዳ ፍላጐት በመቀነሱ ምክንያት በቆዳ ዘርፍ የሚታየውን የኤክስፖርት ንግድ መዳከም ከፍተኛ የጥሬ ቆዳና ሌጦ ብክነት እንዲሁም በከፊል የተዘጋጀ ቆዳና ሌጦ ክምችት ያስከተለ በመሆኑ፣
ይህንን ችግር ለማቃለል ወደውጭ በሚላክ በጥሬና በከፊል በተዘጋጀ ቆዳና ሌጦ ላይ የተጣለወን የታክስ ማስከፈያ ምጣኔዎች ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ፣
የገንዘብ ሚንስቴር በውጭ ገበያ በማቅርብ ጥሬ እና በከፊል የተዘጋጀ ቆዳና ሌጦ ላይ ታክስ ለማስከፈል በወጣው አዋጅ ቁጥር 567/2000 አንቀጽ 4 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አወጥቷል፡፡