የከተማ መሬት ይዞታ ማረጋገጥ እና ምዝገባ መመሪያ ቁጥር 45/2007 ፀድቆ ተግባራዊ ማድረግ ከተጀመረ በጊላ በትግበራ ሂደት ያጋጠሙ ክፍተቶችን ለመፍታት፤ በአንድ አንድ አንቀፆች የተቀመጡ ሃሳቦች ከተጨባጭ ስራው ጋር የተጣጣሙ ለማድረግ፤
የተለየ መመሪያ ሳያስፈልጋቸው በዚህ መመሪያ መካተት ያለባቸውን አዳዲስ የድንጋጌ ክፍሎች ማካተት በማስፈለጉ፤
ከአዋጁና ከደንቡ ጋር ተጣጥመው መቀመጥ የሚገባቸው አንቀፆችም በመኖራቸው እንዲሁም መመሪያው ብዙ ለውጦችን የያዘ በመሆኑ የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባ አዋጅ ቁጥር 818/2005 አንቀጽ 54(2) መሠረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡