የሕገወጥ ዕቃዎች እንቅስቃሴ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ውስብስብ በመሆኑ እና ውጤታማ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ለመሥራት የሕብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፣
ከኮንትሮባንድ፣ ከንግድ ማጭበርበርና ሕገወጥ ዕቃዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በይዘትም ሆነ በመጠን እየተበራከቱና እየተወሳሰቡ በመሄዳቸው በሕጋዊ የንግድ እንቅስቃሴ፣ በመንግሥት ገቢ እንዲሁም በሕብረተሰቡ ደኅንነት ላይ አደጋ እያስከተሉ በመምጣታቸው ይህንን ሕገወጥ ድርጊት በተጠናከረ መልኩ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ስልቶችን መዘርጋት በማስፈለጉ፣
የኮንትሮባንድ እና ሌሎች የጉምሩክ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ መረጃ ወሳኝ በመሆኑና ለዚህም አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ ጠቋሚዎች፣ ያዦች፣ ተባባሪዎችና ደጋፊዎች ካደረጉት ተሳትፎ ጋር የተመጣጠነ ወሮታ ሊከፈላቸው የሚገባ በመሆኑ፣
የሕገ ወጥ ዕቃዎች የወሮታ ክፍያ መጠን ለመወሰን፤የወሮታ ክፍያውን ተፈፃሚ ለማድረግ መሟላት ስለሚገባቸው ቅድመ ሁኔታዎች ለማስቀመጥ እንዲሁም ሌሎች ከወሮታ ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ማካተት በማስፈለጉ፤
የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 622/2ዐዐ1 አንቀጽ 78 (3) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡