የኢትዮጵያ ከይዘን ኢንስቲትዩት የከይዘን የአመራር ፍልስፍናን ከምንጩ በማሸጋገር እና በመተግበር የታቀደውን ዕቅድ በባለቤትነት ክትትል፣ ድጋፍና ግብረ መልስ መስጠት በየደረጃው ያለው አመራር ድርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት ከአቅርቦትና ከግብዓት አንፃር መሟላት የሚገባቸውን በማሟላት ሥራውን ማሳለጥ ተገቢ በመሆኑና ሲሰራበት የነበረው የኃላፊዎችና ሠራተኞች የስልክና የመስተንግዶ መመሪያ መንግሥት ካወጣው መመሪያ አንፃር ማሻሻል አስፈልጓል፡፡
በዚሁ መሠረት ኢንስቲትዩቱ ለዋና ዳይሬክተር እና ለምክትል ዋና ዳይሬክተሮች መደበኛ የመስመር ስልክ፣ የኢቪዲዮ አፓራተስ እና የመስተንግዶ አገልግሎትን እንዲሁም ለዳይሬክተሮች መደበኛ የመስመር ስልክ እና የመስተንግዶ አገልግሎት አጠቃቀም ከኢንስቲትዩቱ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ይህ የውስጥ መመሪያ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡