ተገቢው እውቀትና ክህሎት ያላቸው የውጭ አገር ዜጎች ኢትዮጵያ ውስጥ በዜጎች ሊሸፈኑ በማይችሉ የሙያ መስኮች እና በአመራር ደረጃ በመሰማራት ተተኪ ኢትዮጵያዊያንን የሚያፈሩበትና ለሀገሪቱ የእውቀትና የቴኮኖሎጂ ሽግግር አስፈላጊውን አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር በማስፈለጉ፣ የሥራ ፈቃድ የተሰጣቸው የውጭ አገር ዜጎች በተፈቀደላቸው የሥራ መስኮችና ድርጅቶች ውስጥ ሕግና ሥርዓትን ተከትለው እየሰሩ መሆኑን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበርና በመቀናጀት ተገቢው ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግበት የተጠናከረ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣ ሚኒስቴሩ ለውጭ አገር ዜጎች የሥራ ፈቃድ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመወሰን ፣ ይህ መመሪያ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡