የመመሪያ መለያ: 852/20114
ቀን: ታኅሣሥ 17፥ 2015 ዓ.ም.
Language: Amharic

የዱር እንስሳት አደን አጠቃቀም የተሻሻለ መመሪያ ቁጥር 852/2014

የዱር እንስሳት ሃብት ባልተቀናጀና አግባብነት በሌለው አጠቃቀም ምክንያት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተመናመነና ለአደጋ ተጋላጭነቱ እየጨመረ በመምጣቱ፤

የዱር እንስሳት አደን አጠቃቀም የዱር እንስሳቱን ህልውና አደጋ ላይ የማይጥልና ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በፍጆታዊ የአጠቃቀም ስልት አማካይነት ከዱር እንስሳት ሃብት የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም በማጎልበት ዘርፉ ለሀገሪቱ ልማት የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ ማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በዱር እንስሳት አደን አጠቃቀም የሚስተዋሉ የአሠራር ክፍተቶችን በማስወገድ ወጥነት፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነትና ፍትሃዊነት የሰፈነበት የአሠራር ሥርዓት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤

ቀደም ሲል የወጡትን የዱር እንስሳት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 541/1999 እና የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር163/2001 ማስፈጸሚያ መመሪያ ማውጣት በማስፈለጉ፤

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር541/1999 አንቀጽ 17 (2) በተደነገገው መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር

Ministry of Culture and Tourism

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration