የመመሪያ መለያ: 697/2013
ቀን: የካቲት 1፥ 2003 ዓ.ም.
Language: Amharic

በተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም እና ሌሎች የመንግስት ፕሮጀክቶች ለተመረጡ ሥራ ተቋራጮች የተሻሻለ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ለመስጠት የወጣ መመሪያ (መመሪያ ቁጥር 697/2013)

የተቀናጀ የቤቶች ልማት ኘሮግራም እና መሰል አገር አቀፍ ሽፋን ያላቸው የመንግሥት ኘርጀክቶች የሥራ ተቋራጮች እጥረት እንዳይገጥማቸው ለማድረግ ባለሙያዎችን መርጦ ለሥራ ተቋራጭነት ለማብቃት በተዘጋጀው ፕሮግራም መሠረት መመሪያ በማዘጋጀት፣ ባለሙያዎችን በመመዝገብ፣ በመምረጥ፣ በማሰልጠን እና ትስስር በመፍጠር ቁጥራቸው ከ750 በላይ የሚሆኑ ባለሙያዎች ወደ ሥራ መግባታቸው እና የሚያበረታታ አፈፃፀም የተመዘገበ መሆኑ ይታወቃል።

የተጠቀሰው ቁጥር ያላቸው ሥራ ተቋራጮች የተመረጡት በአገር አቀፍ ደረጃ በተጀመሩት እና በመከናወን ላይ በሚገኙት ለተቀናጀ የቤቶች ልማት ኘሮግራም፤ ለጤና ጣቢያዎች ግንባታ፣ ለቴሌኮም የሞባይል ማስፋፊያ ኘሮጀክቶች፣ ለሬዲዮ ማስፋፊያ ፕሮጀክት፣ ለተንዳሆ ስኳር የቤቶች ልማት ኘሮጀክት እንዲሳተፉ ታስቦ የነበረ ሲሆን በዚህም የተነሣ ሥራ ተቋራጮቹ እንዲያገኙ የተደረገው የምስክር ወረቀት ተሳትፏቸውን በነዚህ ግንባታዎች ብቻ የሚወሰን ነበር። በአሁኑ ጊዜ ሊገነቡ የታቀዱት ጤና ጣቢያዎች በሙሉ ሥራ ተቋራጮች የተመደቡላቸው በመሆኑ፣

የሞባይል ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችም ከአንድ የግንባታ ዙር በኋላ የሚጠናቀቁ በመሆነ እና በቤቶች ልማት ኘሮጀክት የሚሸፈኑ ከተሞች ቁጥር የሚጨምር ባለመሆኑ የተመረጡትን ሥራ ተቋራጮች ከተጠቀሱት ኘሮጀክቶች ጋር ብቻ በማስተሳሰር መቀጠል አስፈላጊ የማይሆንበት ደረጃ ተደርሷል፡፡ ከዚህም የተነሳ ሥራ ተቋራጮቹ በሌሎች የግንባታ ቦታዎችም ተወዳድረው መሥራት የሚቻሉባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት አስፈልጓል፤

በዚህም መሠረት ለተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም እና ሌሎች መሰል የመንግሥት ፕሮጀክቶች ባለሙያዎችን መርጦ ለሥራ ተቋራጭነት ለማብቃት በተዘጋጀው መመሪያ መሠረት የተመረጡት እና ወደ ሥራ የገቡት ባለሙያዎች በማንኛውም ደረጃቸው በሚፈቅድላቸው ፕሮጀክቶች ላይ መሳተፍ እንዲችሉ ለማድረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 691/2ዐዐ3 አንቀጽ 25/1/ ሥር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

Ministry of Urban and Infrastructure

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration