የተቀናጀ የቤቶች ልማት ኘሮግራም እና መሰል አገር አቀፍ ሽፋን ያላቸው የመንግሥት ኧርጀክቶች የአማካሪ ድርጅቶች እጥረት እንዳይገጥማቸው ለማድረግ – ባለሙያዎችን መርጦ ለአማካሪነት ለማብቃት በተዘጋጀው ፕሮግራም መሠረት መመሪያ በማዘጋጀት፣ ባለሙያዎችን በመመዝገብ፤ በመምረጥ፣ በማሰልጠን እና ትስስር በመፍጠር ቁጥራቸው ከ40 በላይ የሚሆኑ አማካሪ አሃዶች ወደ ሥራ መግባታቸው እና የሚያበረታታ አፈፃፀም የተመዘገበ መሆኑ ይታወቃል፡፡ የተጠቀሰው ቁጥር ያላቸው አማሪ አሃዶች የተመረጡት በአገር አቀፍ ደረጃ በተጀመሩት እና በመከናወን ላይ በሚገኙት ለተቀናጀ የቤቶች ልማት ኘሮግራም፣ ለጤና ጣቢያዎች ግንባታ፤ ” ለቴሌኮም የሞባይል ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች፣ ለሬዲዮ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ለተንዳሆ ስኳር የቤቶች ልማት ኘሮጀክት እንዲሳተፉ ታስቦ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ሊገነቡ የታቀዱት ጤና ጣቢያዎች አብዛኛዎቹ አማካሪዎች የተመደቡላቸው በመሆኑ፣ የሞባይል ማስፋፊያ ኘሮጀክቶችም ከአንድ የግንባታ ዙር
በኋላ የሚጠናቀቁ በመሆኑ እና ቤቶች ልማት ፕሮጀክት የሚሸፈኑ ከተሞች ቁጥር የሚጨምር ባለመሆነ የተመረጡትን አማካሪ ድርጅቶች ክተሱት ፕሮጀክቶች ጋር ብቻ በማስተሳሰር መቀጠል አስፈላጊ የማይሆንበት ደረጃ ተደርሷል፤ ከዚህም የተነሳ አማካሪ አሃዶች በሌሎች ቦታዎችም ተወዳድረው መሥራት የሚችሉባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት አስፈልጓል፡፡ በዚህም መሠረት ለተቀናጀ የቤቶች ልማት ፕሮግራም እና ሌሎች መሰል የመንግሥት ፕሮጀክቶች ባለሙያዎችን መርህ ለእረፍት ተረት የተመረጡት እና ወደ ሥራ የገቡት አሃዶች በማናቸውም ደረጃቸው በሚፈቅድላቸው ፕሮጀክቶች ላይ መሳተፍ እንዲችሉ ለማድረግ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 691 2003 አንቀጽ 25 1 ሥር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡