የፌደራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሠረት የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በአዲስ መልክየተቋቋሙ ሲሆን ኮሚሽኑም ለሚኒስቴሩ ተጠሪ ሆኖ በመደራጀቱ ለዚህ ለውጥ ውጤታማነት ተገቢውን ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በሥራ ላይ ያለው የተቋሙ የተፈላጊ ችሎታ መስፈርትና የሥራ ልምድ አያያዝ ማኑዋል አሁን ያለውን የአደረጃጀት ለውጥ እንዲያካትት በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል፣ የታክስ/ጉምሩክ አስተዳደር ሥራን በአግባቡ ለማከናወን እንዲያመች ለማድረግ በሚኒስቴሩ ሠራተኞች አስተዳደር ደንብ ቁጥር 155/2000 አንቀጽ 45 ለሚኒስቴሩ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡