የመመሪያ መለያ: 899/2014
ቀን: ግንቦት 1፥ 2014 ዓ.ም.
Language: Amharic

የሃይማኖት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ፈቃድ አሠጣጥ መመሪያ ቁጥር 899/2014

በሳተላይት ወይም በኬብል አማካኝነት የሚሰራጭ የሃይማኖት ብሮድካስት አገልግሎት የሃይማኖት ተቋማት አስተምህሮታቸውን በብሮድካስት ጣቢያዎች ለማድረስ እንዲሁም በማኅበራዊ ጉዳዮች፣ በሰላም ግንባታ፣ በሥነ-ምግባር ዕሴቶች፣ በታሪክ እና መሰል ሃይማኖታዊ እሴቶች ዙሪያ ማሕበረሰቡን ለማስተማር፤ ህብረተሰቡም ባለበት ቦታ ሆኖ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞችን ለመከታተል እንዲችል፤ የሃይማኖት ብሮድካስት ጣቢያዎችም ሃይማኖታዊ ሚናቸውን በተገቢው መንገድ እንዲጫወቱ ለማስቻል፤

የሃይማኖት ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ አሰጣጥ ሂደትን ግልጽ እና ፍትሃዊ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤

በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 6(1)፣(5) እና 40(3)(ለ)፤ መሠረት የሀይማኖት ብሮድካስት አገልግሎት የፈቃድ አመልካቾች ፈቃድ ለመስጠት እንዲሁም ባለፈቃዶች ሕገ መንግስቱን፣ የአገሪቱን ሕጎች እንዲሁም፤ የሕዝብን ሰላም፣ ደኅንነት፣ የዜጎችን ተነፃፃሪ መብቶችና ጥቅሞች ባከበረ መልኩ በኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤

በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 12(7) እና አንቀጽ 90(2) መሠረት ይህ መመሪያ በባለሥልጣኑ ቦርድ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን

Ethiopian Media Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration