ኢትዮጵያ የፈረመችውን የህዋ አጠቃቀም ሀብቱን ለሰላማዊ ግልጋሎት ለማዋል እና የእኩል ተጠቃሚነት መብት እንዲኖራቸው የሚያደርገውን የOuter Space Treaty ስምምነት አክብሮ ከዘርፉ የላቀ ጥቅም ለማስገኘት የተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎን ማረጋገጥ ጎን ለጎን ከስፔስ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ጋር ተያይዘው ከሚመጡ አሉታዊ ተጽእኖዎች ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድ በማስፈለጉ፤ የስፔስ የቁጥጥር ስርዓት ለስፔስ ሥራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን መመዝገብ፣ በግል ይዞታ ሥር የሚገኙ ሳተላይቶችንም ሆነ የሳተላይት መረጃዎችንና ምልክቶችን ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ጨምሮ አዘገጃጀቱንና ስርጭቱን፣ አጀማመሩንና የሚከናወነውን ሥራ መምራት ለማስቻል፤
በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንስትትዩት ደንብ ቁጥር 393/2009 አንቀጽ 10 ን/አንቀጽ (10) የክትትልና የቁጥጥር ስራ እንዲያከናውን በተሰጠው ሥልጣን ከዓለም አቀፋዊ ግዴታዎች ጋር በተያያዘ የስፔስ ዘርፉን ለሰላማዊ ዓላማ መጠቀምን ማረጋገጥን ጨምሮ በስፔስ ጉዳዮች ላይ የተሰማሩ ተቋማትን በመመዝገብ፣ ፈቃድ በመስጠት፣ በማደስ፣ ማሻሻያ በማድረግ እና እንዳስፈላጊነቱ ፈቃድ የሚቋረጥበትን የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት ማስተዳደር አስፈላጊ በመሆኑ፤
የስፔስ ቁጥጥር ስርዓትን አስመልክቶ በሕግ እና በፖሊሲ የተቀመጡ የማስፈፀሚያ ስትራቴጂዎችን ስራ ላይ ለማዋል እንዲቻል የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 10 ንዑስ አንቀጽ (2) መሠረት ይህንን የስፔስ ቁሶች ምዝገባ ኢንስፔክሽን ቁጥጥርና ፈቃድ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡