በማንኛውም ተቋም የሪከርድና ማህደር ሥራ ዋና ዋና ከሚባሉት የአስተደደር ሥራዎች አንዱ ነው፡፡ በመሆኑም በከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ስር በአግባቡ የተደራጀ የሪከርድና ማህደር መኖሩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የተጣለበትን የሥራ ድርሻና ኃላፊነት ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ የሚጫወተው ሚና እጅግ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ግልጽና ተጠያቂነት ያለበት አሠራር በማስፈን፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ አገለግሎቶች በመስጠት የሚኖረው ድርሻ የላቀ ነው፡፡
የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የሪከርድ ሥራ አመራር አሁን ያለውን የመዝገብ አያያዝ እና አደረጃጀት ዘመናዊ በሆነ አሠራር በመተካት ለአገልግሎት አሰጣጥ በሚያመች ሁኔታ እንደገና አጥንቶ ማደራጀቱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመፃህፍት ኤጀንሲ በሪከርድ ሥራ አመራርና በመዛግብት አስተዳደር የተሰጠውን ሥልጠናና በሌሎች መ/ቤቶች ተሞክሮ በመውሰድ እንዲሁም ቀደም ሲል ሲሰራበት የነበረውን የጉዳይ ማውጫ መሠረት በማድረግ እና ሚኒስቴር መ/ቤቱ በሚያከናውናቸው ተግባራት አማካይነት የሚፈጠሩትን የሪከርዶች አፈጣጠር፣ አመዳደብ፣ አደረጃጀት፣ ቁጥጥር፣ ጥበቃና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም አወጋገድ ዘመናዊ ለማድረግ ይቻለው ዘንድ ይህን በሥራ ሂደት የሚጎለብት የሪከርድና ማህደር ሥራ አመራር የውስጥ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
በአጠቃላይ ይህ የሪከርድ ሥራ አመራር የአሠራር ስርዓት መመሪያ የመስሪያ ቤቱን የስራ እንቅስቀሴ የሚደግፍና ለመስሪያ ቤቱ ስራ አመራር ፈጣን ዉሳኔ ለመስጠት የሚያግዝ፣ የተገልጋዮችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ፣ ትክክለኛ፣ ፈጣን መፍትሄ፣ የመሠረታዊ የስራ ሂደት ገቢና ወጪ ደብዳቤ በተጠናው መሠረት ስታዳርድ መሠረት ተፈፃሚ እንዲሆን እና ወሳኔ ለመስጠት የሚረዳ፣ የጊዜን፣ የንብረት እና የአገልግሎት ጥራትን በአስተማማኝ ሁኔታ ለማምጣት እንደ መሳሪያ ሆኖ የሚገለግል ነው፡፡