በካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2014 ሰነደ ሙዓለ-ንዋዮች ለሕዝብ ሽያጭ የማቅረብ እና የግብይት መስፈርቶችን የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን
በመመሪያ እንዲወስን የተደነገገ በመሆኑ፤
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የካፒታል ገበያ ሥርዓት ያለው፣ ፍትሐዊ፣ ቀልጣፋ እና ግልጸኝነት የሰፈነበት መሆኑን የሚያረጋግጥ፣ የኢንቨስተሮችን
ጥቅም የሚያስጠብቅ፣ ውጤታማና ቀልጣፋ የሆነ ለሕዝብ ሽያጭ የማቅረብና የሰነድ ሙዓለ-ንዋይ ግብይት እንዲኖር የሚያደርግ እና
የካፒታል ገበያ እድገትን የሚያስፋፋ የቁጥጥር ማዕቀፍ መኖር አስፈላጊ በመሆኑ፤
ባለሥልጣኑ በአዋጁ አንቀጽ 75፣ 76፣ 77 እና 108(2) ድንጋጌዎች መሠረት ይህንን ለሕዝብ ሽያጭ የማቅረብ እና የሰነድ ሙዓለ-ንዋይ ግብይት መመሪያ አውጥቷል።