ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የወጣባቸው የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶችን የሚለሙበትና የሚተዳደሩበት መመሪያ የሌለው በመሆኑ በሀብቶቹ ላይ በርካታ ችግሮች ማለትም ስርቆት፣ በተሽከርካሪ ግጭት ምክንያት በመሰረተ ልማቶች ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን፣ በግለሰብና በመንግሥት ተቋማት የሚቀርቡ የይነሳልን ቅሬታዎችን ለመፍታት፣ የአገልግሎት ጥራትና ደረጀ ለማሻሻል፣ የጥገና አሠራር ስርዓት ለመዘርጋት፤
የተገነቡና እና በቀጣይ የሚገነቡ የሕዝብና ጭነት ትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ደህንታቸው የተጠበቀ፣ ንጽህ፣ ምቹና ዘላቂ ሆነው ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ፤
ከፍተኛ የመንግሥት ወጪ ወጥቶባቸው የተገነቡና በቀጣይ የሚገነቡ መሰረተ ልማቶች የአገልግሎት ዘመናቸውን ለማሳደግ፣ የግንባታና የጥገና ወጪዎችን ለመቀነስ፣ ሀብቶችን በላቀ ደረጃ ለማስተዳደር፣ የህብረተሰቡን የእርካታ ደረጃ ለማሳደግ፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ለማጠንከር፣ የሌሎች የመንገድ ተጠቃሚዎችን ደኅንነት ለመጠበቅ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ ወጥ የሆነ የአጠቃቀምና የአስተዳደር ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላት እንደገና ለማደራጀት ሥልጣንና ተግባራቸውን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 74/2014 ዓ.ም አንቀጽ 15 ንዑስ አንቀጽ (2) ተራ ፊደል (ሠ) መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡