በመሠረታዊ ሸቀጥነት ከተለዩ ምርቶች ውስጥ የምግብ ዘይት አንዱ በመሆኑ ከህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ጋር ተገናዝቦ ፣ የተጣራ ምግብ ዘይት አቅርቦት፣ ስርጭት እና ዋጋ ቁጥጥር እየተደረገበት ለህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ አስመጪዎችን መምረጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ሃገሪቱ ከዉጭ አገር በመንግሥት ድጎማ የምታስመጣዉ የምግብ ዘይት በሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎች በማምረት ቀስ በቀስ የምግብ ዘይት ፍላጎት ማሟላት እና ከአቅርቦት እስከ ስርጭት ያለውን የንግድ ሰንሰለት ቁጥጥርና ድጋፍ ለማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በዘርፉ ተሳታፊ የሚሆኑትን ተዋናዮች የመምረጥ ሂደት ላይ ግልጽነት እንዲኖረው ማድረግ፣ እንዲሁም ከልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች እና በተዋረድ የሚገኙ የአስተዳደር አካላት ተሳትፎ አስፈላጊነት የታመነበት በመሆኑ፤
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢፌዲሪ አስፈጻሚ አካላት ተግባርና ሥልጣን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 ዓ.ም እንቀጽ 19(1-በ) መሠረት ለማስፈጸም ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡