የመመሪያ መለያ: 997/2016
ቀን: መጋቢት 23፥ 2016 ዓ.ም.
Language: Amharic

ፕሮግራሞችን ለደንበኞች በክፍያ የማቅረብ አገልግሎት መመሪያ ቁጥር 997/2016

የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ለሀገራችን አድማጭ ተመልካቾች በአማራጭነት የሚቀርቡበትን መንገድ በማመቻቸት የዜጎችን የመረጃ፣ የመዝናኛ እና የትምህርት ፍላጐት ማሟላት አስፈላጊ በመሆኑ፤

በውጭ ሀገር ወይም በሀገር ውስጥ የተዘጋጁ የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች በሀገራችን ለሚገኙ አድማጭ ተመልካቾች በክፍያ የሚቀርቡበትን እና ዘርፉ በሕግ የሚመራበትን አሠራር መዘርጋት በማስፈለጉ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 30 መሠረት ፕሮግራሞችን ለደንበኞች በክፍያ የማቅረብ አገልግሎት ሥራ ለመሠማራት የብሮድካስት ፈቃድ ማግኘት በማስፈለጉ እና የፈቃድ አሰጣጥ ሒደቱን ግልፅ፣ ፍትሐዊ፣ አሳታፊ እና ተደራሽ ማድረግ በማስፈለጉ፤

በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 6(1)፣(5)፤ እና 31(1)(ሐ) መሠረት ፕሮግራሞችን ለደንበኞች በክፍያ የማቅረብ አገልግሎት ስራ ላይ ለመሠማራት የሚፈልጉ አመልካቾች በመመሪያው የተቀመጡ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን በማረጋገጥ ፈቃድ መስጠት፣ ዘርፉን ማስፋፋት፣ ለሕብረተሰቡ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ማመቻቸት እንዲሁም ባለፈቃዶች ሙያዊ ሥነ-ምግባርን፣ ሕገ መንግስቱን፣ የሀገሪቱን ሕጎች እንዲሁም የሕዝብን ሰላም፣ ደኅንነት፣ የዜጎችን ተነፃፃሪ መብቶች እና ጥቅሞች ባከበረ መልኩ በኃላፊነት ስሜት ሥራቸውን ማከናወናቸውን ማረጋገጥ በማስፈለጉ፤

በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 12(7) እና አንቀጽ 90(2) መሠረት ይህ መመሪያ በባለሥልጣኑ ቦርድ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን

Ethiopian Media Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration