የመመሪያ መለያ: 660/2013
ቀን: ኅዳር 1፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የሙያ መሰላልን የጠበቀ የደረጃ ዕደገት ማወዳደሪያ መስፈርት (መመሪያ ቁጥር 660/2013)

በአየር ትራፊክ ቁጥጥር፣ በመገናኛ ናቪጌሽን ቅኝት ምህንድስና መሣሪያዎችና በኤሮኖቲካል መረጃ አገልግሎት ባለሙያዎች ከመለስተኛ የሥራ ደረጃ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የሥራ ደረጃ ድረስ በቅድሚያ የአቪዬሽን ዘርፉን እድገት ተከትሎ በሚሰጥ የረጅም ወራት ሙያዊ የክህሎት ሥልጠና በንድፈ ሀሳብ የሲሙሌሽን/የተግባር/ እና /OT/የሥራ ላይ ሥልጠና ወጤታቸው አመርቂ ሆኖ ሲገኝ ሙያ መላልን የጠበቀ እድገት መስጠቱን አጠናክሮ ለማቀጠል፣

የኦፕሬሽናልና ቴክኒካል የሥራ መደቦችን የሚሰጠው ሥልጠና ዓይነትና ደረጃ መለየትና ቀደም ብሎ ሙያዊ ክህሎት የማስጨበጡ ተግባር በመፈፀም ባለሙያው በተፈለገ ጊዜ የተሃድሶ ሥልጠና በመስጠት ሙያውን መሠረት በማድረግ እንዲሰራ ለማስቻልና ተተኪን ለማፍራት፣

በአየር ትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች በየደረጃው የሚሰጠውን ሥልጠና በአጥጋቢ ሁኔታ ፈፅመዋል ማለት የሚለቻው በሰለጠኑበት ሙያ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሙያ ምዘና/rating ተደርገው ሰርቲፋይድ/ብቃታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ብቻ ካገኙ በኃላ የሙያ መሰላልን የጠበቀ እድገት ለመስጠት የምዘናና ከእድገቱ ጋር ተያያዥ ክፍዎችን ለመፈፀም በወጣ መመሪያ መሠረት ለመፈፀም፣

የአየር ትራፊክ ቁጥጥር ባለሙያዎች በየደረጃው ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና በቅጥር በማስገባት እስከ 18 (አስራ ስምንት) ወራት አፕሮች አየር ትራፊክ ቁጥጥር ድረስ በማሰልጠን ሥልጠናውን በየደረጃው ማለትም በንድፈሀሳብ የሲሙሌሽን/የተግባር/እና OT/የሥራ ላይ በስኬት ካጠናቀቁ በኃላ ዓለምአቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የሙያ ምዘና/rating ሰርቲፋይድ/ብቃታቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ላገኘ/ች የደረጃ እድገቱ ለመስጠት እንዲቻል፣

ባለሙያው የሙያ ሥልጠና ወስዶ የሙያ መሰላል የጠበቀ የደረጃ እድገት ለመስጠት በተለይም ከቅርንጫፍ ጽ ቤት ተወዳድረው ለሥልጠና የሚመጡ ባለሙያዎች እስከ ስምንት ወራት ድረስ ስለሚቆዩ ምደባቸው ሥልጠናው እስኪጠናቀቅ በምን መልኩ መሆን እንደሚገባው ቀደም ሲል በአሠራርና በመመሪያ ባለመካተቱ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የሕግ ድጋፍ ለማግኘት፤

የኢንተርናሽናል ኤርፖርቶች ተግባራት እየሰፋ በመምጣቱና የባለሙያ የምደባ ስብጥርና ደረጃውም ያለውን ትራፊክ ለማስተናገድ በሚቻል መልኩ እያሰለጠኑ መመደብ ስለሚገባ በቀድሞ የሥልጠና አሰጣጥ መርሐግብር መሠረት የሰለጠኑ ባለሙያዎች በዋናው መ/ቤት በየደረጃው የሚሰጠውና እስከ ስምንት ወራት በሥልጠና ቆይተው የሙያ መሰላልን በጠበቀ የደረጃ እድገት ከአንዱ የሥራ ጣቢያ ወደሌላ የሥራ ጣቢያ የሚመደቡ ባለሙያዎች የአመዳደብ ሁኔታን መወሰን ስለሚገባ፣

ሥልጠናው በውድድር ላይ ተመስርቶ የሚፈፀምና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ባለሙያዎችን ስለሚያካትት በየደረጃው በሚሰጥ ሥልጠና ውስጥ ለመሳተፍ በቅድሚያ ማሟላት የሚያስፈልገውን መመዘኛና ግልጽ የማወዳደሪያ መስፈርት ማዘጋጀት እና መራጭ ኮሚቴ በሚሰጠው ውሳኔ መሠረት ብልጫ ያላቸውን ባለሙያዎች መርጦ ማሰልጠን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

የሙያ መሰላልን የጠበቀ ሥልጠና ተከታትሎ በአጥጋቢ ሁኔታ ያጠናቀቀ ባለሙያ በክፍት የሥራ መደብ ላይ በደረጃ እድገት ወደ ከፍ ወዳለው የሙያ መሰላል የሚመደብበትን የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የባለሥልጣኑ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ብቃትን ማዕከል ያደረገ፣ ግልጽ፣ ፍትሃዊና ከአድሎ የፀዳ እንዲሆንና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲፈጸም ለማድረግ ታስቦ ይህ ማወዳዳሪያ መስፈርት ተዘጋጅቷል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን

Ethiopian Civil Aviation Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration