በባለሰልጣን መ/ቤቱ የግዥ ፍላጎትን መሠረት በማድረግ የሚገዙ ግዥዎችን ግልፅ፣ ቀልጣፋ ውጤታማ እና ከኪራይ ሰብሳቢነት በፀዳ መልኩ የተሳለጠ የግዥ አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻል በማስፈለጉ፤
የሚታዩ የግዥ አፈፃፀም ችግሮችን በማስወገድ የመንግሥት የግዥ ስርዓት ይበልጥ ግልፅ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊና አድሎ የሌለበት እንዲሁም ለግዥ የሚውለውን ከፍተኛ የመንግሥት ገንዘብ ቁጠባንና ውጤታማነትን ማረጋጋጥ በሚያስችል መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
የመንግሥት ንብረት ለከተማ አስተዳደሩ የተሻለ ጥቅም በሚያስገኝ አኳኋን ጥቅም ላይ እንዲውል እና አስተዳደሩም የተቀናጀ ስርዓት ሊዘረጋ እንደሚገባ የታመነበት በመሆኑ፤
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደርን ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 17/2002 እና የግዥ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2002 የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ለማስፈፀም ይህን የግዥ ሂደት መመሪያ አውጥቷል፡፡