የመመሪያ መለያ: 450/2013
ቀን: ታህሳስ 21፥ 2012 ዓ.ም.
Language: Amharic

የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 450/2013

ሀገራችን በተለያዩ ተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት የመኖሪያ አካባቢያቸውን በመተው ጥላና ከለላ በመፈለግ ለሚመጡ ስደተኞች ለሚመጡ መሠረታዊና ማኅበራዊ ግልጋሎት ከመስጠት በተጨማሪ ያላቸውን ችሎታና እምቅ አቅም በመጠቀም ወደ ስራ ገብተው ለራሳቸውና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲያበረክቱ እንዲሁም ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ወቅት የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ ለማድረግ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ስምምነቶችን በመፈፀም የሚገኘውን ገንዘብ በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ የኤጀንሲው ዋነኛ ተግባር ነው።

ይህንኑ አገልግሎት ለመስጠት በሚደረገው የገንዘብ እንቅስቃሴ የሚፈፀም የዕቃና አገል ግሎት ግዥ አፈፃፀም አግባብነት ያለው እንዲሆን በማድረግ የተገኘው ሪሶርስ የስደተኛውን ፍላጎት እንዲያረካ የሚደረገው ጥረት የአገርን መልካም ገፅታ ከመገንባት አንፃር የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ቀላል ሆኖ አይታይም።

ኤጀንሲው ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የሚገለገልበት የዕቃና የአገልግሎት ግዢ መመሪያ ያለው ቢሆንም በግዜው እየጨመረ ያለውን የስደተኛ ፍላጎት ካለው በጀት ጋር ሊጣጣም የሚችል ቀልፍ ፡ የማትሰርዓት ለመፍጠር፣ ተለዋዋጭ የሆነ የገበያ ዋጋ ሁኔታን ታሳቢ ለማድረግ፣ተቋሙ አዲስ የአደረጃጀት ለውጥ በማድረጉ እና አልፎ አልፎ በስራ ላይ እያጋጠሙ ያሉ የአፈፃፀም ችግሮችን ሊፈታ የሚችል የተሻሻለ መመሪያ በማስፈለጉ በሥራ ላይ ያለው መመሪያ፣ የመንግሥት የግዢ መመሪያ ፣ የUNHCR እና ተመሳሳይ ድርጅቶችን የግዥ አፈጻጸም መመሪያ እንደግብዓትነት በመጠቀም የኤጀንሲውን ተልዕኮ ለማስፈጸም በሚያስችል መልኩ ተሻሻሎ እንዲቀርብ ተደርጓል።

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የኢፌዲሪ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት

FDRE Refugees and Returnees Service

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration