የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን በአዋጅ ቁጥር 10/87 እና በአዋጅ ቁጥር 35/2004 እንዲሁም በደንብ ቁጥር 34/94 የተቋቋመለትን ዓላማ ውጤታማ በሆነ መልክ በመፈፀም ደንበኞች ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ ውጤታማና ፍትሀዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤
ዉሳኔ የሚያስፈልጋቸዉን የተለያዩ ጉዳዮች ሕግና ስርዓትን በተከተለ መልኩ እንዲከናወኑ ለማስቻል የባለስልጣኑን ፕሮሰስ ካውንስል ተግባርና ኃላፊነት በግልፅ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤
የኘሮሰስ ካወንስሉ ወቅቱንና ጊዜውን የጠበቀ የሥራ ዕቅድ እንዲያዘጋጅ በማድረግና አፈፃፀሙን ተከታትሎ በመገምገም በተቋሙ ውጤታማ የሆነ የሥራ አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻል እንዲሁም ስራውን ኃላፊነትና ተጠያቂነት ባለው መንገድ ለመምራት እንዲችል ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ስለታመነ፤
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡