አገራችን ሇዘመናት ስደተኞችን ተቀብሊ በማስተናገዴ ቀዯምት ታሪክ ያሊት አገር ስትሆን በአሁኑ ወቅትም ከፍተኛ ቁጥር ያሇው ስዯተኛ በተሇያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች አስጠሌሊ ትገኛሇች፡፡
መንግሥት የስዯተኞችን ጉዲይ አለማቀፋዊ ባህሪ ያለው መሆኑን በመረዳት በአለማችን እየሰፋ ያለውን የተፈናቃዮች እና ስዯተኞች ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንዱሁም ስዯተኞች ለአንድ ሀገር ሸክም ሳይሆኑ እንደ ሀብት በመቁጠርም የልማት አጋር እንዲሆኑ በማስቻል እና በስደተኛ መጠለያ ጣቢያ አካባቢዎችም ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል መንግሥት ከዚህ በፊት በስራ ሊይ የነበረውን የስደተኛ ሕግ በማሻሻል አዋጅ ቁጥር 1110/2011 እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
አዋጁም ስደተኞችን ወደ ስራ በማስገባት የተለያዩ የሀገሪቷ ህጎችን ያጣጣመ እንዲሆን ከመደረጉም ባሻገር ስደተኞች መንግሥት ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጋር በመተባበር የጋራ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ወደ ስራ የሚሰማሩበትን እንዲሁም የውጭ ሀገር ዜጎች የተፈቀደ የስራ ዘርፎች ላይ ስደተኛው የስራ ፈቃድ በማውጣት መሥራት ስለሚቻልበት ሁኔታ ይደነግጋል፡፡
በመሆኑም ይህ አዋጅ በሀገሪቷ ያልነበረውን አዱስ የስደተኞች አያያዝ በተሻለ ሁኔታ ያስቀመጠና በዚህ ሕግ ውስጥ ህጉን ለመፈፀም ስደተኞች ከወጭ ሀገር ዜጎች በተሸለ የሚስተናገዱበትን አሠራር የዘረጋ ቢሆንም አዋጁ አዲስ እንደመሆኑ መጠን ስደተኛው በግሌ፣ በቅጥር እንዱሁም በጋራ ሊሰማሩባቸው በሚችሉ ስራዎች ላይ ግልፅ የሆነ የአሠራር ስርዓትና የሕግ ማዕቀፍ ባለማስቀመጡ ምክንያት አዋጁን ለማስፈጸም ወሳኝ የሆኑ የአጋር አካላትን በማሳተፍ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡