የመመሪያ መለያ: 515/2013
ቀን: ጳጉሜ 1፥ 2008 ዓ.ም.
Language: Amharic

የልማት ድርጅቶችና አክስዮን ማህበራት የፕራቬታዜሽን ክፍያ አሰባሰብ መመሪያ ቁጥር 515/2013

ሚኒስቴር መ/ቤቱ በተለያዩ የፕራይቬታይዜሽን ስልቶች የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን/አክሲዮን ማህበራትን ወደ ግል አልሚዎች በማዛወር ውጤታማ ሥራ እያከናወነ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ከፕራቬታይዜሽን ፕሮግራም ጋር የተያያዙ የተለያዩ ክፍያዎችን በቅልጥፍና በግልጽነትና ተጠያቅነት በሰፈነበት አሠራር ለመሰብሰብ የሚያስችል መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በተለይ ድርጅቶቹ ወደ ግል አልሚዎች የሚተላለፉት በውል ላይ ተመስርቶ በሙሉ ክፍያ ወይም በተራዘመ ክፍያ /differed payment/ በመሆኑ የሽያጭ ክፍያውንም ሆነ የርክክብ ልዩነት ትመና ክፍያ በተቀላጠፈና በግልጽ አሠራር ለመሰብሰብ እንዲቻል በመመሪያ መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ፣

በመንግሥት እጅ የነበሩ አክሲዮን ማህበራት ወደ ግል አልሚዎች ከመተላለፋቸው በፊት በተለያዩ የማስፋፊያ ፕሮጄክቶች እንዲሁም የሚያጋጥማቸውን የስራ ማስኬጃ ችግር ለማቃለል ከኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ በውል ላይ የተመሰረተ የብድር አገልግሎት እንዲያገኙ የሚደረግ በመሆኑ እንዲሁም ባተረፉት መጠን የመንግሥት ትርፍ ድርሻ የሚከፍሉ የሚደረግ በመሆኑ ድርጅቶቹ የተበደሩትን ክፍያ እና የነበረባቸውን የመንግሥት ትርፍ ድርሻ ሳያጠናቅቁ ወደ ግል አልሚዎች በሚዛወሩበት ወቅት ያለባቸውን እዳ ገዢው እንዲከፍል በውለታ ለነዱ እንዲካተት የሚደረግ በመሆኑ የክፍያውን አሰባሰብ በግልጽ ማስቀመጥ አስፈለጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የአስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916 /2008 አንቀጽ 31 (1)(ለ) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የመንግስት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር

Ministry of Public Enterprises

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration