የመመሪያ መለያ: 464/2013
ቀን: የካቲት 1፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የዕጽዋት ዘር ግብይት ማስፈጸሚያ (መመሪያ ቁጥር 464/2013)

የተሻሻለ የዕጽዋት ዝርያ ዘር ግብይት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው:: በሀገራችን ለበርካታ ዓመታት ሲተገበር የቆየው የዕጽዋት ዘር ግብይት ሥርዓት የተራዘመ የዘር ግብይት ሰንሰለት ያለው፣ የተጠያቂነት ሥርዓት የጎደለው እና መንግሥትን ከፍተኛ የሆነ ገንዘብና የሰው ሃይል ሲጠይቅ የቆየ ነው:: በመሆኑም መንግሥት የነባሩን የዕጽዋት ዘር ግብይት አሠራር ማነቆዎችን መፍታት የሚያስችል የቀጥታ ዘር ግብይት ሥርዓት በሙከራ ደረጃ ሲተገብር ቆይቷል፡፡ የቀጥታ ዘር ግብይት ሥርዓት የዘር አምራች ድርጅቶች ያመረቱትን ዘር ተጠያቂነት ባለው መልኩ በራሳቸው የሽያጭ ወኪል በቀጥታ ለተጠቃሚው በመሸጥ የዕጽዋት ዘርን ከአማራጭ ምንጮች በወቅቱ፣ በሚፈለገው ዓይነት፣ በጥራት፣ በቦታ እና በመጠን እንዲያገኝ በማድረግ የሚያድርን የዘር መጠን ወሳኝ በሚባል መልኩ ቀንሷል፡፡

የቀጥታ ዘር ግብይት ጠቃሚ ተሞክሮዎችን በመቀመርና አገራዊ ፋይዳ ያላቸውን አሴቶችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የዕጽዋት ዘር ግብይት ተወዳዳሪነት የሰፈነበት እና ገበያ ተኮር እንዲሆን ለማድረግ እንዲቻል በዕጽዋት ዘር አዋጁ 782/2005 እና በደንብ ቁጥር 375/2008 መሠረት ይህን የዕጽዋት ዘር ግብይት መመሪያ ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የግብርና ሚኒስቴር

Ministry of Agriculture

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration