የመንቀሳቀስ ችግር ያለባቸው አካል ጉዳተኞች በተሽከርካሪ በመታገዝ ከቦታ ወደቦታ በመንቀሳቀስ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተገቢውን ተሳትፎ በማድረግ ራሳቸውንና አገራቸውን እንዲጠቅሙ መንግሥት ተገቢውን እገዛ ማድረግ እንዳለበት በመታመኑ፣
አካል ጉዳተኞች ወደ አገር የሚያስገቧቸው ልዩ ተሽከርካሪዎች ከማናቸውም ቀረጥና ታክስ ነፃ ሆነው እንዲገቡ የተሰጠው መብት ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ የሚያስችል ዝርዝር የአፈፃፀም መመሪያ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
የገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ሥልጣን መሠረት ይህን መመሪያ አውጥቷል፡፡