የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርናው ክፍል ኢኮኖሚምትና ምርታማት ለማሳደግ ቴክኖለጂ በማመንጨት፣ በማሳደግና በማስረጽ ረገድ ቀደምሲል የደረሰበትን የላቀ የእድገት ደረጃ በማጠበቅ ለተሻለ ስኬት በጽናት እየሠራ ነው፡፡
ኢንስቲትዩቱ የተማሪዎችን እወቀትና ክህሎት በተሻለ ብቃት ለመጠቀም ከሚለገልባቸው ስልቶች አንዱ ለምርምሩ ሥራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ተሜዎች ምርምሩ በሚሄድበት አካባቢ በቅርበት በር የምርምሩን ሥራ በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያከናውኑ የመኖሪያ ቤት በተገነ ባላቸው ዕከላት የመኖሪያ ቤት አገልግሎት እንደተቋሙ ሠራተኛ ምድብ (ተመራማሪና ድጋፍ ሰጭ) ማቅረብ ነው፡፡ ኢንስቲትዩቱ ተማሪዎችን ለማረታታትና ለማጋት እንዲቻል ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ያቀረበው አዲስ የደመዘ ማሻሻያና ጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ በመንግሥት ጸድቆ ከግንቦት 1 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንዲጣል ተደርጓል፡፡
ይህ የደመወዝ ማሻያና ጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ መኖሪያ ቤት ላልተሰጣቸው የመኖሪያ ቤት አበልን የካተተ በመሆኑ ከነሐሴ 2ዐዐ4 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረውን የመኖሪያ ቤትና ማልገያ ዕቃዎች ድልድልና አጠቃቀም መመሪያ በአዲስ መልክ ከለሳና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኗል፡፡