በየጊዜው የሚወጣ የህትመት መገናኛ ብዙኃንን በመላው ኢትዮጵያ ተደራሽ በማድረግ ሕዝብን ለማሳወቅ፣ ለማስተማርና ለማዝናናት እንዲሁም የሕዝብን መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ ከማስቻሉ ባሻገር የንባብ ባህልን የሚያዳብር በመሆኑ፤
በየጊዜው የሚወጡ የህትመት መገናኛ ብዙኃንን በአይነትም ሆነ በቁጥር እንዲስፋፉ ማድረግ፤ የዜጎችን የሃሳብና የአመለካከት ብዝኃነት ለማስተናገድ እንዲሁም የአገራችንን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና የሚጫወት በመሆኑ፤
በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 26 መሠረት በየጊዜው በሚወጣ የህትመት መገናኛ ብዙኃን ለመሠማራት መመዝገብ እና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ማግኘት በማስፈለጉ እና የምዝገባ ሒደቱን ግልፅ፣ ፍትሐዊ፣ አሳታፊ እና የሃሳብና የመረጃ ብዝኃነትን የሚያስፋፋ ማድረግ በማስፈለጉ፤
በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 6(3) እና 6(5) መሠረት በየጊዜው የሚወጡ የህትመት መገናኛ ብዙኃንን ማስፋፋት፣ መደገፍና መከታተል በማስፈለጉ፤
በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 አንቀጽ 12(7) እንዲሁም አንቀጽ 90(2) መሠረት ይህ መመሪያ በባለሥልጣኑ ቦርድ ወጥቷል፡፡