የመመሪያ መለያ: 522/2013
ቀን: ግንቦት 9፥ 2011 ዓ.ም.
Language: Amharic

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት አመራሮች፣ ኢንስትራክተሮች እና አሰልጣኞች የሥራ ላይ ሥልጠና አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 522/2013

የሥራ ላይ ሥልጠና በሥራ ላይ የተሰማሩ ወይም እንዲሰማሩ የታሰቡ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት አመራሮች፣ ኢንስትራክተሮች እና አሰልጣኞች ከተግባርና ኃላፊነታቸው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ወይም አግባብነት ባላቸው ልዩ ልዩ ሙያዎች በማሰልጠን የተሰማሩበትን ወይም የሚሰማሩበትን የሥራ አመለካከት፣ ዕውቀትና ክህሎት እንዲያሻሽሉ ማድረግ እና እንደ አገር ወጥ የሆነ የስራ ላይ ትምህርትና ሥልጠናን መምራት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት ወሳኝ በመሆኑ፤

በሥራ ላይ ትምህርትና ሥልጠና በሚያገኙት እውቀትና ክህሎት የሥራ ችሎታቸውን አሻሽለው በተመደቡበት ሥራ ወይም ኃላፊነት ላይ የተሻለ የሥራ ውጤት ለማስገኘት እንዲቻል እንዲሁም በሙያ መሰላል ላይ ተመስርቶ ለበለጠ ኃላፊነት የሚያበቃቸው ዝግጅት እንዲኖራቸው ማድረግ በማስፈለጉ፤

በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና አዋጅ ቁጥር 954/2003 አንቀጽ 43/3 እና የፌዴራል መንግሥት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባርን ለመወሰን በወጣ አዋጅ ቁጥር 1097/2011 አንቀጽ 26 ለሚንስቴሩ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህ መመሪያ ወጥቷል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

Ministry of Science and Higher Education

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration