የመመሪያ መለያ: 26/2013
ቀን: ግንቦት 2፥ 2013 ዓ.ም.
Language: Amharic

የትርፍ ሰዓት ስራ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 26/2013

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በከተማው አስተዳደር ም/ቤት መጋቢት 6 ቀን /1990 ዓ.ም በደንብ ቁጥር 7/1990 ዓ.ም ሲቋቋም ዋነኛ ዓላማው በከተማዋ ማስተር ፕላን መሠረት ደንብና ስርዓት ጠብቆ ዋና ዋና መንገዶች፣ እግረኛ መንገዶች ፣ ድልድዮች፣ የፈሳሽ ማስወገጃ መስመሮች እና የመሳሰሉት ዲዛይን እንዲያወጣ፣ እንዲገነባ፣ እንዲያስገነባ፣ እንዲጠግንና እንዲያስተዳድር ለማስቻል ነው፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ የህብረተሰቡን ፍላጎት ደረጃ በደረጃ ለማርካት፣ ከተማዋ የአፍሪካ መዲና እንዱሁም የዓለም ዓቀፍ ተቋማትና ዲፕሎማት መኖሪያ እንደመሆኗ መጠን ደረጃቸውን የጠበቁ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታውን አጠናክሮ ማስቀጠል ዋነኛው ተግባር ይሆናል፡፡

የመንገድ መሰረተ ልማቱ የከተማዋን የልማትና ዲሞክራሲ ማዕከል በማድረግ አገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ ለማሰለፍ የሁለተኛውን ዙር የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የቀጣይ 5 ዓመታት (2008 – 2012) ዓ.ም የመንገድ ልማት ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ መረባረብ ይጠይቃል፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱም የከተማው ሕዝብና አስተዳደሩ የጣለበትን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እንዳያስችለው በአዲስ መልክ ያልተማከለ አደረጃጀት በመፍጠር ወደ ተግባር እንቅስቃሴ ገብቷል፡፡ በዚህም የመንገድ ልማት ስራው በባህሪው በመደበኛ የስራ ስዓት ክንውን ብቻ ውጤታማ መሆን እንደማይችል ቢታመንም፣ የትርፍ ስዓት ስራ ክፍያ በአፈፃፀም ላይ መሠረት ያደረገ /PERFORMANCE RELATED PAYMENT/ ባለመሆኑ የአሠራር ክፍተቶች ይታዩበታል፡፡

ከዚሁ በተጨማሪ አሁን በተፈጠሩት አዲስ አደረጃጀቶች ከዚህ ቀደም በነበረው የትርፍ ሰዓት ክፍያ አሠራር መመሪያ ያልተካተቱ በመሆኑ፣ እንዲሁም የስራ ክፍሎች በመንገድ ልማት ስራው ያላቸው ተሳትፎ በግልፅ ያልታዬ በመሆኑ በአፈፃፀም ስራዎች ላይ ችግር እያጋጠመ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት የመደበኛውን የስራ ስዓት ባገናዘበ መልኩ የወሩ ትርፍ ስዓት ካልተወሰነ ከባለስልጣኑ ዋና ዋና ወጪዎች በበለጠ ሁኔታ ትልቁን የወጪ ድርሻ ይዞ ሊገኝ እንደሚችል አያጠራጥርም፡፡ በመሆኑም የባለሥልጣን መ/ቤቱን በጀት በዕቅድ ይዞ በመምራት አሰራራችን ግልፀኝነት፣ ተጠያቂነትና ወጥነት ያለው እንዲሆን ለማስቻል የትርፍ ስዓት ስራ አፈፃፀም መመሪያ ማሻሻል አስፈሊጊ ሆኖ በመገኘቱ ይህ መመሪያ ተሻሽሎ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡

PDF Document

Tap the button below to view or download this PDF.

View PDF

ተጨማሪ መረጃዎች

መመሪያውን ያውርዱ

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

Addis Ababa City Roads Authority

Similar Directives

ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration
ሰኔ 18÷2018
ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
Ministry of Trade and Regional Integration